የችግኝ መያዣ ከረጢት

የችግኝ መያዣ ከረጢት


የችግኝ መያዣ ከረጢት ከፖሊቲን የሚሰራና ጥቁር መልክ ያለው ሲሆን ችግኙ በተፈላጊው ሥፍራ ደርሶ እስኪተከል ድረስ ለማቆየት የሚያገለግል ነው፡፡ ከሌሎች የችግኝ ማቆያ ዘዴዎች አንጻር ስናነጻጽረው የችግኝ መያዣ ከረጢትን መጠቀም ወጪ ቆጣቢ ሲሆን የችግኙም ስሮች ለእድገት እንዲነሳሱ ከመርዳቱም በተጨማሪ በአንድ ስኩዌር ፉት የሚኖሩትን ተክሎች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ አል ቁድስ ኩባንያ የደንበኞቹን ፍላጎት የሚያሟሉ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የችግኝ መያዣ ከረጢቶች ያቀርባል፡፡