በማዳበሪያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን

በማዳበሪያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን


የፖሊቲን ቁስን ለእርሻ ሥራ መጠቀም የተክሎች እድገት እንዲፋጠን ከመርዳቱም በተጨማሪ የሰብል ብዛትን ለመጨመር ያግዛል፡፡ የፕላስቲክ ሽፋን ማዳበሪያን መጠቀም ተክሎችን ለማሳደግ አንዱ መንገድ ሲሆን በዚህ ሂደትም ከፖሊቲን የተሰራውን የፕላስቲክ ሽፋን ለተክሉ የሚሆን ቀዳዳ ብቻ በመተው በማሳው ላይ በማንጠፍ መጠቀም ይቻላል፡፡

በመልች ፕላስቲክ መጠቀም ጤናማ የሆኑ ሰብሎችን በከፍተኛ መጠን ለማምረት ያስችላል፡፡ ይህ አሰራር ካሉት በርካታ ጠቀሜታዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

  1. በመልች ፕላስቲክ መጠቀም እርጥበትን ለመጠበቅ የሚያስችል በመሆኑ ለተክሎች የሚቀርበውን የውሃ አቅርቦት ለማሳደግ ያስችላል፡፡
  2. የመልች ፕላስቲክ የተክሎች ሥር ከሙቀትና ከቅዝቃዜ ለመታደግ ያስችላል፡፡
  3. የአረም እድገትን ይቀንሳል፡፡
  4. የአፈር ገጽታን ለመሸፈን ያገለግላል፡፡
  5. አፈርን ከጀርሞች ነጻ ለማድረግ ያስችላል፡፡
  6. የአፈር እርጥበትን ይጠብቃል፡፡
  7. እንደ እንጆሪ ያሉ ፍራፍሬዎች ንጽህና እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡

አል ቁድስ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የማልች ፕላስቲክን በተለያዩ ቀለማት ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡ ከእነዚህ ቀለማት መካከል በጥቁር፣ ግልጽ ውሃ ቀለም፣ በቢጫ፣ በውህድ ቀለሞች፡-ብርማ እና ጥቁር፣ ነጭና ጥቁር፣ ብርማና ቡኒ ይጠቀሳሉ፡፡ ከ70 እስከ 180 ሳሜ ስፋትና ከ30 እስከ 50 ማይክሮን ውፍረት ገደብ ውስጥ የሚገኙ የማልች ፕላስቲክ ምርቶችንም ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡

 

*ባለ 35 ማይክሮን የውፍረት መጠን ያለው ለእርሻ አገልግሎት የሚውል የማልች ጥቅል 

ኤከር/ቶን ኪግ/ኤከር ሜትር/ቶን ስፋት
15.4 ኤከር 65 ኪግ 34000 ሜትር 90 ሳሜ
14.3 ኤከር 70 ኪግ 31000 ሜትር 100 ሳሜ
12.5 ኤከር 80 ኪግ 2800 ሜትር 110 ሳሜ
11.1 ኤከር 90 ኪግ 25500 ሜትር 120 ሳሜ
8.7 ኤከር 115 ኪግ 19000 ሜትር 160 ሳሜ
7.7 ኤከር 130 ኪግ 17000 ሜትር 180 ሳሜ