የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚረዳ የፕላስቲክ ሽፋን

የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚረዳ የፕላስቲክ ሽፋን


የከፋ የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚዘጋጀው የፕላስቲክ ሽፋን በአብዛኛው የሚሰራው ዝቅተኛ እፍግታ ካለው የተጣጣፊ ላስቲክ(ፖሊቲን) ቁስ ነው፡፡ እነዚህን መሰል መሸፈኛዎች የሚያገለግሉት ተክሎች ለምግብ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸው ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተክሎቹ አካባቢ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ ነው፡፡ የፕላስቲክ ሽፋኑም በግማሽ ክብ ቅርጽ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን ይህም ተክሎች የሚያስፈልጋቸውን የጸሃይ ጨረር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚረዳ የፕላስቲክ ሽፋን ጠቀሜታ

  • የሎው ታናል ፕላስቲክ የተክል ለጋ ቅርንጫፍ በተለይም በአሸዋማ አፈርና አሸዋማ የአየር ጸባይ ውስጥ በጎርፍ እንዳይጠቃ ይከላከላል፡፡
  • ተክሎችን ከተለያዩ እንደ ከፍተኛ ነፋስ፣ ዝናብ፣ ቀዝቃዛ ወጀብ ወ.ዘ.ተ ያሉ የአየር ንብረት ተጽእኖ ይከላከላል፡፡
  • የምርት መድረሻ ግዜን ከማፋጠኑ በተጨማሪ ከፍተኛ ጥራትና በገበያ ላይ ተፈላጊ የሆነ ምርት ለማምረት ይረዳል፡፡
  • ለእርሻ የሚውሉ ጸረ ተባይ ኬሚካሎችን መጠቀም ያስቀራል፡፡
  • የፕላስቲክ ሽፋንን ከማይጠቀሙ እርሻዎች በተሻለ የውሃ ድርቀትን ይቀንሳል፡፡
  • ከእጸዋት ማሳደጊያ ፕላስቲክ ይልቅ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችልና ወጪ ቆጣቢ ነው፡፡
  • የውኃ ትነትን በመቆጣጠርና ተስማሚ የእርጥበት መጠንን በመጠበቅ የመስኖ አጠቃቀምን ለማሳደግ ያስችላል፡፡
  • ጥቅም ላይ የሚውለው ሎው ታናል ፕላስቲክ የጸሃይ ብርሃንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳለፍ ስለሚችል የተክሎቹ የምግብ አዘገጃጀት ሂደትን ለማሳደግ በዚህም የተነሳ የምርቱን ጥራት ለማሳደግ ያስችላል፡፡

*አል ቁድስ ኮርፖሬሽን የ220 ሴንቲ ሜትር ስፋት እና ከ40-80 ማይክሮን ውፍረት ያለውን የሎው ታናል ፕላስቲክ ለገበያ ያቀርባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በደንበኞች ጥያቄ መሰረት የተፈለገውን ያህል ስፋትና ውፍረት ያላቸውን የሎው ታናል ፕላስቲክ ማቅረብም ይችላል፡፡

*ለእርሻ የሚውል 220 ሴ.ሜ.  ስፋት ያለው የሎው ታናል ጥቅል

ኤከር/ቶን ኪ.ግ/ኤከር ሜትር/ቶን ውፍረት
2.75 ኤከር 270 ኪ.ግ 6000ሜትር 80 ማይክሮን
3.25 ኤከር 315 ኪ.ግ 7000 ሜትር 70 ማይክሮን
3.70 ኤከር 270 ኪ.ግ 8150 ሜትር 60 ማይክሮን
4.45 ኤከር 225 ኪ.ግ 9800 ሜትር 50 ማይክሮን
5.60 ኤከር 180 ኪ.ግ 12250 ሜትር 40 ማይክሮን