የእጸዋት ማሳደጊያ ከለላ መስሪያ ፕላስቲክ

አዲሱ የማምረቻ መስመራችን ለተክሎች ማብቀያና ማራቢያ ቤት የሚውል ፕላስቲክን ለማምረት የሚችል የዘመነ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ነው፡፡ ይህም የደንበኞቻችንን የግሪን ሀውስ ፕላስቲክ ልዩ መስፈርቶችን ማሟላት የሚያስችል ጠቀሜታ ያለውና እስከ 16 ሜትር ስፋት በመያዝ የሚመረት እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምርት ነው፡፡

የፕላስቲክ ሽፋን ምርታችን የውፍረት መጠኑን ይዞ የሚዘልቅ ነው፡፡ ይህም ዘላቂ የሆነ ጥራት፣ የብርሀን አስተላላፊነትና ንፁህ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህም ባለ 5 ንብርብር የማምረቻ መስመር  የፕላስቲክ ሽፋን ማምረት የሚያስችል ነው፡፡ የማምረቻ መስመሩ ማንኛውንም አይነት በፕላስቲክ ሽፋኑ ላይ ሊጨመሩ የሚችሉ ግብአቶችን ማካተት የሚያስችልና በዕፀዋት ማብቀያ የፕላስቲክ ቤት ውስጥ ለሚበቅሉ ማንኛውም ዓይነት ተክሎች ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠር ዋስትናን ይሰጣል፡፡

በዚህም የተሻለ ለእርሻ አገልግሎት የሚውል የፕላስቲክ ሽፋን በተቀመጠው የአገልግሎት ዘመን ያለምንም ችግር ሜካኒካዊ ባህሪውን ሳይለቅ ይቆያል ማለት ነው፡፡ የምናመርተውን የፕላስቲክ ሽፋን ውፍረት በማሳነስም ተመሳሳይ የአገልግሎት ዘመን እና ሜካኒካዊ ባህሪን የያዘ ነገር ግን ወጪን የቀነሰና ከፍተኛ የግብርና ምርት ለሚሰጡ ሰብሎችንም መጠቀም ይቻላል፡፡

 

የአል-ቁድስ የእፀዋት ማሳደጊያ ፕላስቲክ ሽፋኖች (Al-Quds Greenhouses Plastic Films):

የአል-ቁድስ የእፀዋት ማሳደጊያ ቤት የሚውለው ሽፋን ዋና ተግባሩ በማራቢያው ውስጥ የሚገኘውን ውስጣዊ አካባቢ (የውጫዊውን የማይመቹ ሁኔታዎች) መጠበቅና መቆጣጠር ነው፡፡ ተገቢ ውስጣዊ የአካባቢ ቁጥጥር የተሻለና ጥራት ያለው የሰብል ምርት ለማስገኘት ያግዛል፡፡ የእፀዋት ማሳደጊያና ማራቢያ ቤት(ለአትክልቶች ፣ ፍራፍሬዎችና አበባዎች) እድገት ተስማሚን አካባቢ ይፈጥራል፤ እፀዋት ሊጎዳቸው ከሚችሉ ዝናብ፣ ነፋስና ቀዝቃዛ የአየር ፀባይ ተጠብቀው እድገታቸው በተፋጠነ መልኩ እንዲቀጥል የሚያስችል ሚዛኑን የጠበቀ አካባቢ እንዲፈጠርላቸው ያደርጋል፡፡

የአል-ቁድስ የእፀዋት ማሳደጊያ ፕላስቲክ ሽፋን የአገልግሎት ጊዜ ከዋስትና ጋር ከ 1 እስከ 4 አመታት የሚደርሱ ናቸው፡፡ እፀዋትን በማሳደጊያ ቤት ማሳደግ በአመት ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ የአዲስ ትውልድ ምርት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተገቢውን ቀመር በመከተል ከተሰራበት እፀዋቱ የፀሀይ ተፅእኖን እስከ 60 ወራት፤ የብርሀንና የሙቀት ቁጥጥርን ለማድረግና አፀዋቱ እርጥበትንና ጭጋጋማ አየርን እንዲቋቋሙም ያስችላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰልፈርና ክሎሪን የመሳሰሉ ኬሚካሎች እንዲቋቋሙ ያግዛቸዋል፡፡ የፀሀይ ተፅዕኖን መቋቋሚያ ጊዜ፣ የፕላስቲክ ውፍረትና ሌሎች በአማራጭ የሚያዙ ተጨማሪዎች የእፀዋት ማሳደጊያ ሽፋኑ ለሚያስፈልጋቸው እፀዋቶች (ለአትክልቶች ፣ ፍራፍሬዎችና አበባዎች) ባህላዊ እርሻ፣ እፀዋትን ከአፈር ይልቅ በውሀ ላይ እንዲበቅሉ ማድረግ፣ ጂኦተርማል አጠቃቀም ወዘተ… በሚኖራቸው ሁኔታና የአካባቢ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ነው፡፡

በእፀዋት ማሳደጊያና ማራቢያ የአል-ቁድስ ተጨማሪ ውህዶች (Al-Quds additives on Greenhouses):

በአብዛኛው ጊዜ በሚመረጡ የእፀዋት ማሳደጊያ ቤት ፕላስቲክ ሽፋኖች ላይ ለሰብል ምርት ተስማሚነት ከመጨመር ባሻገር ለሌሎች ተግባራት የሚያገለግሉ ተጨማሪ ውህዶች  ይካተታሉ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ልዕለሀምራዊ UV- Ultra-violet ፡- ይህ የፕላስቲክ ሽፋን የፀሀይ ጨረርን እንዲቋቋም የሚረዳ መቆጣጠሪያ ነው፡፡ ይህ የፀሀይ ጨረር መቆጣጠሪያ ልዕለሀምራዊ (UV) መጠን በጭማሪነት ጥቅም ላይ እንዲውል የሚወስነው የዕፅዋት ማሳደጊያ ቤት ሽፋን እድሜን፣ የሽፋኑን ውፍረት ፣ የምንጠቀመውን ፀረ-ተባይ መጠን ፣ ሽፋኑ ጥቅም ላይ የሚውልበት አካባቢብ የአየር ንብረት ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ይሆናል፡፡

qqq

I am text block. Click edit button to change this text. Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

I am text block. Click edit button to change this text. Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.