የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ የፕላስቲክ ጥቅል

የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ የፕላስቲክ ጥቅል


የእርሻ ፕላስቲክ እርሻን ለመሸፈን የሚያገለግል ሆኖ የዘመኑን የፕላስቲክ ምርት ቴክኒክና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ የያዙ ቁሶችን በማምረቻ ግብአትነት በመጠቀም የሚመረት ነው፡፡ እነዚህን መሰል የእርሻ መሸፈኛዎች የሚመረቱት በተለየ መንገድ ተግባራዊ የሚደረግ ተያያዥነት ያለው ሥርዓት ውስጥ በማለፍ ሲሆን በጥናትና ምርምር የተገኙ ተጨማሪ ግብአቶችም ጥቅም በመዋላቸው ከፍተኛ ጥራት ያለው ፖሊቲን ለማስገኘት ይረዳል፡፡

እነዚህ ምርቶች ከ3 ሜትር እስከ 3 ነጥብ 5 ሜትር ስፋትና እስከ 120 ማይክሮን ውፍረት ያላቸውን የወይን እርሻዎች ለመሸፈን ያገለግላሉ፡፡ የወይን እርሻን በፕላስቲክ መጋረድ ወይን፤ በተለይም ዘር አልባ የወይን ዓይነቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያድጉ ከሚያስችሉ አሰራሮች ሁሉ የተሻለው አሰራር ነው፡፡ በፕላስቲክ ያልተጋረደ ወይንን ከተጋረደው ጋር ስናነጻጽር፤ ወይንን መጋረድ ምርቱ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲደርስ ከማስቻሉም በተጨማሪ የወይን ዘለላዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ያስችላል፡፡ በዚህም መሰረት የፕላስቲክ መሸፈኛን የሚጠቀሙ የወይን አምራቾች ከፍተኛ ጥራት የጠበቁ ምርቶችን ያለምንም ችግር ማምረት እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡