ስለ እኛ ተቋም

ስለ እኛ ተቋም

ድርጅታችን አል-ቁድስ ለፕላስቲክ ከተመሰረተበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2002 ጀምሮ   ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በማምረት ረገድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ድርጅት ሲሆን፡፡  የድርጅተችን ምርቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃን የያዙ ናቸው፡፡ ከምርቶቻችን መካከል ፡- የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ ጥቅል ፕላስቲክ ፣ ለእርሻ መፋሸሻነት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶች፣ ለማዳበሪያ ማስተላለፊያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን፣ ሙዝን እንዳይበላሽ የሚከላከል ከረጢት እና የችግኝ መያዥያና ማስቀመጫ ከረጢት ናቸው ከዚህም በተጨማሪ በራሳቸው ሀይል መኮማተር የሚችሉና ለመጠቅለያነትና ማሸጊያነት የሚያገለግሉ ምንም ቀለም ከሌለው ጀምሮ በ6 ዓይነት የቀለም ምርጫዎች የተዘጋጁ የፕላስቲክ ውጤቶች እናቀርባለን፡፡

ራዕይ

To be one of the globally leading and preferred companies  in the  agricultural plastic supplies world.

ተልዕኮ

ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በማቅረብ በዘርፉ በዓለም ላይ ቀዳሚና ተመራጭ ከሆኑ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሆኖ መገኘት፡፡

ምርቶቻችን

icon

የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚረዳ የፕላስቲክ ሽፋን

የከፋ የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚዘጋጀው የፕላስቲክ ሽፋን በአብዛኛው የሚሰራው ዝቅተኛ እፍግታ ካለው የተጣጣፊ ላስቲክ(ፖሊቲን) ቁስ ነው፡፡ እነዚህን መሰል መሸፈኛዎች የሚያገለግሉት ተክሎች ለምግብ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸው ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተክሎቹ አካባቢ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ ነው፡፡ የፕላስቲክ ሽፋኑም በግማሽ ክብ ቅርጽ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን ይህም ተክሎች የሚያስፈልጋቸውን የጸሃይ ጨረር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

icon

በማዳበሪያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን

የፖሊቲን ቁስን ለእርሻ ሥራ መጠቀም የተክሎች እድገት እንዲፋጠን ከመርዳቱም በተጨማሪ የሰብል ብዛትን ለመጨመር ያግዛል፡፡ የፕላስቲክ ሽፋን ማዳበሪያን መጠቀም ተክሎችን ለማሳደግ አንዱ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም ከፖሊቲን የተሰራውን የፕላስቲክ ሽፋን ለተክሉ የሚሆን ቀዳዳ ብቻ በመተው በማሳው ላይ በማንጠፍ መጠቀም ይቻላል፡፡

የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ የፕላስቲክ ጥቅል

የእርሻ ፕላስቲክ እርሻን ለመሸፈን የሚያገለግል ሆኖ የዘመኑን የፕላስቲክ ምርት ቴክኒክና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ የያዙ ቁሶችን በማምረቻ ግብአትነት በመጠቀም የሚመረት ነው፡፡

የሙዝ ማቆያ ከረጢቶች

የሙዝ ምርት ለመድረስ በአማካይ 8 ወራትን ይወስዳል፡፡ ሙዝ ለመብቀል ሙቀታማና እርጥበት ያለበትን የአየር ጸባይ ይመርጣል፡፡

የችግኝ መያዣ ከረጢት

የችግኝ መያዣ ከረጢት ከፖሊቲን የሚሰራና ጥቁር መልክ ያለው ሲሆን ችግኙ በተፈላጊው ሥፍራ ደርሶ እስኪተከል ድረስ ለማቆየት የሚያገለግል ነው፡፡

ለመጠቅለያና ማሸጊያ የሚያገለግሉ ከረጢቶችና ጥቅሎች

አል ቁድስ ኮርፖሬሽን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ከረጢቶችና ጥቅሎችን ያመርታል፡፡ እነዚህ ምርቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃና የአገልግሎት ግዜ ያላቸውም ናቸው፡፡

ደንበኞቻችን