የአል ቁድስ ገለጻ


Al Quds Description

አል ቁድስ ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ቁሶችን ለማምረት የሚጠቀመው ግብአት የመጨረሻውን የቴክኖሎጂ ደረጃ የያዙ ናቸው፡፡ ምርቶቹም ተገቢውን የምርት ደረጃ ጠብቀው ማለፋቸው በፍተሻ ይረጋገጣል፡፡ ይህም መተግበሩ የተቋሙ ምርቶች ተገቢውን የአገልግሎት ግዜ ጠብቀው እንዲቆዩ፣ ሳይበጠሱ እንዲወጠሩ የሚያስችል ጥንካሬ እንዲኖራቸው፣ ተገቢውን ውፍረት እንዲይዙ፣ ማንኛውንም የአየር ጸባይ እንዲቋቋሙና ጎጂ የጸሃይ ጨረርን በማስወገድ ጠቃሚ የሆነው ብቻ ወደ ተክሎቹ እንዲደርስ የማድረግ አቅምን እንዲጎናጸፉ አስችሏቸዋል፡፡ ለዚህም ነው የአል ቁድስ የፕላስቲክ ምርቶች ለተጠቃሚዎች ምርጡ ምርጫ ነው የምንለው፡፡

icon

የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ የፕላስቲክ ጥቅል

እነዚህ ምርቶች ከ3 ሜትር እስከ 3 ነጥብ 5 ሜትር ስፋትና እስከ 120 ማይክሮን ውፍረት ያላቸውን የወይን እርሻዎች ለመሸፈን ያገለግላሉ፡፡ የወይን እርሻን በፕላስቲክ መጋረድ ወይን፤ በተለይም ዘር አልባ የወይን ዓይነቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያድጉ ከሚያስችሉ አሰራሮች ሁሉ የተሻለው አሰራር ነው፡፡ በፕላስቲክ ያልተጋረደ ወይንን ከተጋረደው ጋር ስናነጻጽር፤ ወይንን መጋረድ ምርቱ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲደርስ ከማስቻሉም በተጨማሪ የወይን ዘለላዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ያስችላል፡፡ በዚህም መሰረት የፕላስቲክ መሸፈኛን የሚጠቀሙ የወይን አምራቾች ከፍተኛ ጥራት የጠበቁ ምርቶችን ያለምንም ችግር ማምረት እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡

icon

የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚረዳ የፕላስቲክ ሽፋን

የከፋ የአየር ጸባይና ተባይን ለመከላከል የሚዘጋጀው የፕላስቲክ ሽፋን በአብዛኛው የሚሰራው ዝቅተኛ እፍግታ ካለው የተጣጣፊ ላስቲክ(ፖሊቲን) ቁስ ነው፡፡ እነዚህን መሰል መሸፈኛዎች የሚያገለግሉት ተክሎች ለምግብ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸው ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተክሎቹ አካባቢ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ ነው፡፡ የፕላስቲክ ሽፋኑም በግማሽ ክብ ቅርጽ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን ይህም ተክሎች የሚያስፈልጋቸውን የጸሃይ ጨረር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

በማዳበሪያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን

የፖሊቲን ቁስን ለእርሻ ሥራ መጠቀም የተክሎች እድገት እንዲፋጠን ከመርዳቱም በተጨማሪ የሰብል ብዛትን ለመጨመር ያግዛል፡፡

የሙዝ ማቆያ ከረጢቶች

የሙዝ ምርት ለመድረስ በአማካይ 8 ወራትን ይወስዳል፡፡ ሙዝ ለመብቀል ሙቀታማና እርጥበት ያለበትን የአየር ጸባይ ይመርጣል፡፡

የችግኝ መያዣ ከረጢት

የችግኝ መያዣ ከረጢት ከፖሊቲን የሚሰራና ጥቁር መልክ ያለው ሲሆን ችግኙ በተፈላጊው ሥፍራ ደርሶ እስኪተከል ድረስ ለማቆየት የሚያገለግል ነው፡፡

ለመጠቅለያና ማሸጊያ የሚያገለግሉ ከረጢቶችና ጥቅሎች

አል ቁድስ ኮርፖሬሽን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ከረጢቶችና ጥቅሎችን ያመርታል፡፡ እነዚህ ምርቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃና የአገልግሎት ግዜ ያላቸውም ናቸው፡፡

ለግብርና ምርቶች ሽፋን የሚሆን እስከ 5 ንብርብር ያለው


ለግብርና ምርቶች ሽፋን የሚሆን እስከ 5 ንብርብር ያለው (Agricultural Blown Film 5-Layers Line) አዲሱ የማምረቻ መስመራችን ለተክሎች ማብቀያና ማራቢያ ቤት የሚውል ፕላስቲክን ለማምረት የሚችል የዘመነ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ነው፡፡ ይህም የደንበኞቻችንን የግሪን ሀውስ ፕላስቲክ ልዩ መስፈርቶችን ማሟላት የሚያስችል ጠቀሜታ ያለውና እስከ 16 ሜትር ስፋት በመያዝ የሚመረት እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምርት ነው፡፡ የፕላስቲክ ሽፋን ምርታችን የውፍረት መጠኑን ይዞ የሚዘልቅ ነው፡፡ ይህም ዘላቂ የሆነ ጥራት፣ የብርሀን አስተላላፊነትና ንፁህ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህም ባለ 5 ንብርብር የማምረቻ መስመር የፕላስቲክ ሽፋን ማምረት የሚያስችል ነው፡፡ የማምረቻ መስመሩ ማንኛውንም አይነት በፕላስቲክ ሽፋኑ ላይ ሊጨመሩ የሚችሉ ግብአቶችን ማካተት የሚያስችልና በዕፀዋት ማብቀያ የፕላስቲክ ቤት ውስጥ ለሚበቅሉ ማንኛውም ዓይነት ተክሎች ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠር ዋስትናን ይሰጣል፡፡ በዚህም የተሻለ ለእርሻ አገልግሎት የሚውል የፕላስቲክ ሽፋን በተቀመጠው የአገልግሎት ዘመን ያለምንም ችግር ሜካኒካዊ ባህሪውን ሳይለቅ ይቆያል ማለት ነው፡፡ የምናመርተውን የፕላስቲክ ሽፋን ውፍረት በማሳነስም ተመሳሳይ የአገልግሎት ዘመን እና ሜካኒካዊ ባህሪን የያዘ ነገር ግን ወጪን የቀነሰና ከፍተኛ የግብርና ምርት ለሚሰጡ ሰብሎችንም መጠቀም ይቻላል፡፡

ስለ እኛ ተቋም

ድርጅታችን አል-ቁድስ ለፕላስቲክ ከተመሰረተበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2002 ጀምሮ   ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በማምረት ረገድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ድርጅት ሲሆን፡፡  የድርጅተችን ምርቶች ከፍተኛ የጥራት ደረጃን የያዙ ናቸው፡፡ ከምርቶቻችን መካከል ፡- የወይን እርሻን ለመጋረድ የሚረዳ ጥቅል ፕላስቲክ ፣ ለእርሻ መፋሸሻነት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶች፣ ለማዳበሪያ ማስተላለፊያነት የሚያገለግል ስስ የፕላስቲክ ሽፋን፣ ሙዝን እንዳይበላሽ የሚከላከል ከረጢት እና የችግኝ መያዥያና ማስቀመጫ ከረጢት ናቸው ከዚህም በተጨማሪ በራሳቸው ሀይል መኮማተር የሚችሉና ለመጠቅለያነትና ማሸጊያነት የሚያገለግሉ ምንም ቀለም ከሌለው ጀምሮ በ6 ዓይነት የቀለም ምርጫዎች የተዘጋጁ የፕላስቲክ ውጤቶች እናቀርባለን፡፡

አል-ቁድስ ለፕላስቲክ በትኩረት ለግብርና አገልግሎት የሚውሉና ለሌሎችም ማሸጊያነት የሚያገለግሉ ምርጥ የፕላስቲክ ምርቶችን በማምረት በግብፅ ካሉት ኩባንያዎች ግንባር ቀደም መሆን፣ ከፍተኛ የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁ ምርቶችንም ለዓለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ ነው፡፡

ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በማቅረብ በዘርፉ በዓለም ላይ ቀዳሚና ተመራጭ ከሆኑ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሆኖ መገኘት፡፡

ዜናዎቻችን

ደንበኞቻችን

የተለያዩ ሀገራት ደንበኞቻችን

We’d be happy to work with you too!